የWorkSource Oregon (ወርክሶርስ ኦሬገን) ወርክሾፖች

የሥራ ዕድልዎን በWorkSource Oregon ወርክሾፖች ይክፈቱ።

LinkedIn Learning ጋር ያለን አጋርነት ችሎታዎን እና ሥራ የመቀጠር ዕድልዎን የሚያሻሽሉባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ኮርሶችን እንዲያገኙ ያስችልዎታል።
የWorkSource Oregon ወርክሾፖችንና የLinkedIn Learning መገልገያዎችን በመጠቀም፥ በሥራ ፍለጋዎ እና በወደፊት ሙያዎ ላይ ስኬታማ ለመሆን የሚያስችሉ ክህሎቶችና እውቀት ያገኛሉ። በሙያዎ እድገት ላይ ኢንቨስት ለማድረግ እና ብዙ ተወዳዳሪ ባለበት የሥራ ገበያ ውስጥ ጎልቶ ለመታየት ይህ ዕድል እንዳያመልጥዎ። 

LinkedIn Learningን በWorkSource Oregon በኩል እንዴት እንደሚገኝ፦

  1. በ www.imatchskills.org ላይ በነጻ ይመዝገቡ እና የሥራ ፈላጊ ፕሮፋይልዎን ይፍጠሩ ወይም ያዘምኑ። 
  2. LinkedIn Learning ፈቃድ ለማግኘት የአካባቢዎን የWorkSource ማዕከል በስልክ ያግኙ ወይም ከቢሮዎቻችን አንዱን በአካል ይጎብኙ።
  3. የLinkedIn Learning ፈቃድ ሲሰጥዎ፥ በኢሜል ሊንክ ይደርስዎታል። የግልዎ የLinkedIn Learning አካውንት ውስጥ ለመግባት የኢሜል ሊንኩን ይጠቀሙ። 

የLinkedIn Learning ጥቅሞች

LinkedIn Learning ዛሬ ባለው የሥራ ገበያ መወዳደር ለመቻል ከ16,000 በላይ የቢዝነስ፥ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ኮርሶችን ያቀርባል።  LinkedIn Learning በሥራ ፍለጋዎ እና በሙያ እድገትዎ ላይ እንዴት ሊረዳዎት እንድሚችል አንዳንድ የኮርስ ምሳሌዎች እነሆ፦
  • የቃለ መጠይቅ ዝግጅት፦ የወደፊት ቀጣሪዎችን ለማስደመም የተለመዱ የቃለ መጠይቅ ጥያቄዎችን እና ቴክኒኮችን በሚገባ ማወቅ። 
  • የሥራ ልምድ ዝርዝርዎን ማመቻቸት፦ ጎልቶ የሚታይ የሥራ ልምድ ዝርዝር እንዴት መፍጠር እንደሚችሉ እና ለአመልካች መከታተያ ሲስተሞች እንዴት እንደሚያመቻቹ ይማሩ። 
  • የኔትወርኪንግ ስልቶች፦ ሙያዊ ግንኙነቶችን ለማስፋት ውጤታማ የኔትወርኪንግ ክህሎቶች ማዳበር። 
  • የግል ብራንዲንግ፦ በሥራ ገበያ ላይ ለየት ብለው መታየት እንዲችሉ የግል ብራንድ ይፍጠሩ። 
  • የደመወዝ ድርድር፦ ደሞዝንና ጥቅማጥቅሞችን ለመደራደር በራስ መተማመንን ይጎናጸፉ። 
  • የሙያ ሽግግር ድጋፍ፦ ሥራ በሚቀይሩበት ጊዜ ድጋፍ ያግኙ፥ ወደ ሲቪል ሚና የሚመለሱ ውትድርና ውስጥ ያገለገሉን ጨምሮ።
LinkedIn Learning የኮርስ ቪዲዮዎችን በ13 ቋንቋዎች እና በማሺን የተተረጎሙ ሰብታይትሎችን ከ20 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ያቀርባል።  የLinkedIn Learning ኮርሶች ይዘትን በፈለጉት ቋንቋ ለማግኘት በአካውንት ሴቲንግ ውስጥ የቋንቋ ሴቲንግስን ወይም ፕሬፈረንስን መቀየር ይችላሉ። 
 

ስኬታማ የስቴት ማመልከቻዎች ወርክሾፕ

በየሁለት ሳምንቱ ማክሰኞ ከጠዋቱ 10፡30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰዓት

ለኦሬገን ስቴት ሥራዎች ማመልከቻ ማስገባት ይፈልጋሉ?  የኦሬገን ስቴት የሥራ ማስታወቂያዎችን፥ ኤጀንሲዎችን እና የሥራ ምደባዎችን እንዴት መቃኘት እንደሚቻል ለማየት በWorkSource ሠራተኞች የቀረበውን በዚህ በቀጥታ የሚተላለፍ ዌቢናር ላይ ይገኙ።  የሥራ ልምድ ዝርዝርዎን ከሥራ ማስታወቂያ ጋር እንዴት ማጣጣም እንደሚችሉ ይወቁ።

እባክዎን ልብ ይበሉ ይህ ወርክሾፕ በእንግሊዝኛ ብቻ የቀረበ ሲሆን የትርጉም አገልግሎት ግን ሲጠይቁ ሊቀርብ ይችላል። 

ለዚህ ወርክሾፕ በመስመር ላይ ይመዝገቡ።

የOregon Employment Department (OED) (የኦሬገን የሥራ ስምሪት መምሪያ) የእኩል ዕድል ኤጀንሲ ነው።  ሁሉሰው የOED ፕሮግራሞችንና አገልግሎቶችን የመጠቀም ዕድል አለው።  OED በነጻ እርዳታ ያቀርባል።  አንዳንድ ምሳሌዎች፦ የምልክት ቋንቋ እና የቃል ቋንቋ አስተርጓሚዎች፥ በሌሎች ቋንቋዎች የተዘጋጁ ጽሑፎች፥ ብሬይል፥ ትልቅ ሕትመት፥ ኦዲዮ እና ሌሎች ቅርጸቶች።  እርዳታ ከፍለጉ  እባክዎን በ503-947-1670 ይደውሉ። የTTY ተጠቃሚዎች 711 ደውሉ። በተጨማሪም በOED_WSO_Workshops@employ.oregon.gov እርዳታ መጠየቅ ይችላሉ።